Senior Electrician
AZ Pipe Manufacturing
- Job type
- Full-time
- Experience
- Senior
- Category
- Mechanical and Electrical Engineering
Job description
* የዕለቱ በሚከናወኑ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ምርመራ ጊዜ ችግሩን ምንጭ በማውጣት ከነመፍትሔው በዝርዝር ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያቀርባል፤ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ጥገና ያከናውናል፡፡ * ለጥገና የሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዝርዝር መግለጫዎችን (Specifications) በማውጣት ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ * ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራ የሚፈልጉ መሣሪያዎችና የመፈተሻ መሣሪያዎች፣ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሪክ ማቀናበሪያ እቃዎችና ማቴሪያዎች ተለይተው እንዲገቡ ይጠይቃል፤ ማሟላቱንም ያረጋግጣል፡፡ * ድንገተኛና ያልተጠበቁ ብልሽቶችን ወይም በፕሮግራም መሠረት የሚጠበቁ የንክብካቤ ጥገና ሥራዎችን በሚደርሰው የሥራ ግዜ መሠረት ይሠራል፣ ያስተባብራል፤ የመጨረሻ ፍተሻ ያደርጋል፤ በትክክል መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፡፡ * ለመሳሪያው ጥገና የሚደረግ የቴክኒክ ዲዛይን ያወጣል፤ በዚሁ መሠረት የቴክኒክ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ * የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራውን የፈጀውን የሥራ ሰዓት፣ የተጠቃሚውን እቃና የመሳሰሉ ሁኔታዎችን አሳይቶ ሪፖርት ያደርጋል፡፡ * አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ማኑዋልና መመዘኛዎች ሲገቡ ይሳተፋል፡፡ * በማምረቻ መሳሪያዎች ላይ የሚደርሰውን የኤሌክትሮኒክስ ሲስተም፣ የኤሌክትሪክ ክፍሎችና ትራንስፎርመር ክትትል ያደርጋል፡፡ * በኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራ ጊዜ አስፈላጊውን መረጃዎች በማቅረብ በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋል፡፡ * ለዓመቱ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የሚፈልጉ እቃዎችና መለዋወጫዎች ዝርዝር በማዘጋጀት አቅርቦ ያስፈጽማል፤ በግብግብ በሥራ ላይ ይውላል፡፡ * ለሥራ ተጠይቆ ከምርት ውጭ ወይም ውጪ ተገዝቶ ከመጣ እቃዎች/መለዋወጫዎች ከተጠየቀው ጋር ተስማሚ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ልዩነት ሲኖር ለቅርብ ኃላፊው በወቅቱ ያሳውቃል፤ እንዲስተካከሉም ያደርጋል፡፡ * የተበላሹና የተፈቱ እቃዎች እያሰባሰበ ለቅርብ ኃላፊው በማሳወቅ ተገናኝተው በሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉትን በመገንዘብ ለሥራ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ * መሳሪያዎች ሲተከሉ ወይም በተለያየ ምክንያት የይዞታ ለውጥ ሲደረግላቸው የተመደቡትን ዓላማዎች በማስተካከል የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን ያከናውናል፡፡ * በኤሌክትሮኒክስ አጠቃቀምና መምሪያ አጠቃቀም ስላደረሱ አዳዲስ ሁኔታዎች የድርጅቱ ሠራተኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ * በድርጅቱ ውስጥ ሊገኙ የሚችሉትን ጥገናዎች ውጭ ራንክ እንዲሠሩ ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት እያደረገ ሲፈቀድ ተከታትሎ ይሰራል፤ ተሰርተው ሲወጡም ትክክለኛነቱን ፈጥሮ በመረጋገጥ ይረከባል፡፡ * የድርጅቱን የሥራ ደህንነት ሕግ ያከብራል፡፡ * የማምረቻ መሳሪያዎች የጥገናና የንክብካቤ መመሪያን በሥራ ላይ ያውላል፡፡ * አዲስ ቴክኖሎጂን ሊያስተዋውቁ የሚችሉትንና ፈጠራ ሥራ ሊያዳብሩ የሚችሉትን ሁኔታዎች በመምረጥ ለቅርብ ኃላፊው ሐሳብ ያቀርባል፡፡ * ሌሎች ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ተዛማጅ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ መስፈርት፡ - በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ወይም በኢንዱስትሪ ኤሌክትሪሲቲ የቴክኒክ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ፤ በተለይም በ PVC ፋብሪካ ኤክስትሩደር (extruder) ላይ ጠንካራ ዳራ/ልምድ ያለው፤ ስለ PLC እና ኢንቨርተር (Inverter) በቂ እውቀት ያለው፤ እንዲሁም የቅድመ ጥገና እና የችግር ፈቺነት (Preventive maintenance trouble shooting) ክህሎት ያለው።
የሥራ ልምድ፡ - በ PVC ፕላስቲክ ፋብሪካ ውስጥ የሰራ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ።
ጾታ፡ - ወንድ።