ምርት ሱፐርቫይዘር
Daylight Applied Technologies PLC
- Job type
- Full-time
- Experience
- Senior
- Category
- Manufacturing and Production
Job description
የምርት ሱፐርቫይዘር በምርት ክፍል ያሉ ሰራተኞችን በማስተባበር በፈረቃው የሚገኙ ሰራተኞችን በማስተባበርና በመምራት፣ የምርት ማሽኖችን ደህንነት እና ኦፐሬሽን በመከታተልና ውጤታማ በማድረግ፤ አስፈላጊ ግብዓቶችን በወቅቱ በማቅረብ እና በማስተባበር በፈረቃው የተመደበውን ምርት በጥራት እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲመርት ማድረግ እና ማስተባበር ሲሆን የሚከተሉት እና ሌሎች በስራ መዘርዝር የሚሰጡ ስራዎችን ያከናውናል
1. በምርት መምሪያው እቅድ መሰረት በሥሩ ለሚገኙት የምርት መስመሮች እና መካኒክ ኦፕሬተሮች የፈረቃውን የምርት እቅድ ማቀድ፤ለመካኒክ ኦፕሬተሮች እቅዱን በማስገንዘብ ማከፋፈል፤በእቅዱ መሰረት እንዲፈጸም ማድረግ፡፡ 2. የምርት ጥሬ ዕቃ፤የማምረቻ መሣሪያዎች እና በስሩ ያሉትን ሰራተኞች አቀናጅቶ በመምራት በድርጅቱ የተቀመጠውን ዕቅድ እንዲሳካ መከታተል፤መቆጣጠርና መፈፀም፡፡ 3. በፈረቃዉ የምርት ሂደት ለመጀመር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፤የማምረቻ መሣሪያዎች እንዲሁም አምራች የሰው ሀይል እና ሌሎች ለምርት ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ፋሲሊቲዎች የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ 4. በፈረቃው ያሉ የክፍሉ ሰራተኞች በተቀመጠላቸው የስራ መመሪያና/work instruction/ እና የምርት ሂደት መቆጣጠሪያ መስፈርት/production process parameters/ መሰረት ስራቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን መከታተል፤አስፈላጊ ማሻሻያ ሲያስፈልግ ተገቢዉን ሁሉ መፈጸም፡፡ 5. በክፍሉ ውስጥ ያሉ የማምረቻ መሳሪያዎች ሁሉም የሚጠቀሙባቸዉ ሰራተኞች በየደረጃቸዉ በሰነድ ርክክብ መደረጉን፤በአግባቡና በእንክብካቤ መጠበቃቸዉንና መያዛቸውን መከታተል፤በማሽን መካኒክ ኦፕሬተሮች አጠቃቀም ክፍተት የሚፈጠር የማሽን ብልሽት እንዳይኖር ማረጋገጥ፤ሲያጋጥም በፍጥነት አጣርቶ ለቅርብ ኃላፊ ሪፖርት ማቅረብና አስፈላጊዉን የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ፡፡ 6. የምርት ማምረቻ መሣሪያዎች ተደጋጋሚ ብልሽት እንዳያጋጥም ከቴክኒክ እና ኢንጅነሪንግ መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙዎች ጋር በመቀናጀት የታቀደ የቅድመ መከላከል ጥገና ስርዓት እንዲተገበር መከታተል፤የማሽን ብልሽት ሲያጋጥም በጥገና መጠየቂያ በፍጥነት ማሳወቅ እና በፍጥነት እና በጥራት ተጠገኖ ወደ ስራ እንዲመለስ ተገቢዉን ክትትል ማድረግ፤ የምርት ሂደቱ ሳይቆራረጥ የማምረቻ መሣሪያዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ በፈረቃዉ ክትትል ማድረግና መቆጣጠር፡፡ 7. በክፍሉ ውስጥ ያሉ የማምረቻ መሳሪያዎች በተወሰነው የማምረት አቅም መሰረት በሙሉ አቅም እያመረቱ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የማሻሻያ እርምጃዎች በየጊዜው ለምርት መምሪያ ስራ አስኪያጅ እያቀረበ ሲፈቀድ የማሻሻያ ሀሳቡን መተግበር፡፡ 8. የተለያዩ የምርት ዌስትና ዲፌክት በተቀመጠላቸዉ ግብ መሰረት መፈጸማቸውን እና በታቀደው እቅድ መሰረት መተግበራቸውን ማረጋገጥ፤የምርት ዌስትና ዲፌክት አፈጻጸም ከተቀመጠዉ ግብ በታች ሆኖ ሲገኝ መንዔዉን በመለየት እና ከሚመለከታቸዉ መምሪያዎች ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ማሻሻያ እንዲከናወን ማድረግ፣ዉጤታማነቱንም ማገራጋገጥ፡፡ 9. ስለ ማሽኖች ሁኔታ፣የሰው ሃይል፣ ምርታማነትን እና ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለነበራቸው ጉዳዮች የበፊቱ የምርት ሱፐርቫይዘር ከጻፋቸው የሎግ ቡክ ሪፖርት መረጃዎችን ይቀበላል የማስተካከያ እርምጃዎችንም ይወስዳል፣ለቀጣዩ ምርት ሱፐርቫይዘር መረጃን ያስተላልፋል፤ 10. ማንኛውም የፈረቃዉ የስራ እንቅስቃሴ የደህንነት መርሆዎችን የተከተለ እንዲሆን ያደርጋል፤የፈረቃዉ ሰራተኞች ተገቢዉን የደህንነት መሳሪያዎችን በስራ ቦታ ላይ እየተጠቀሙ መሆናቸዉን ያረጋግጣል፤የደህንነት መርሆዎችን የሚጻረሩ እና የሚጥሱ፤የተሰጣቸዉን የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች በአግባቡ የማይጠቀሙ ሰራተኞች ላይ አስፈላጊዉን የማስተካከያ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡፡ 11. የፈረቃዉ ሰራተኞችን የስራ አፈጻጸም በድርጅቱ የአፈፃፀም መመሪያ መሰረት መረጃዎችን በማደራጀት በየወሩ አፈጻጸም መሙላትና ለሰራተኞች ግብረመልስ ይሰጣል፤በዓመት ሁለት ጊዜ የሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም በማጠቃለል ሞልቶ ለምርት ስራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡ 12. በድርጅቱ የሚተገበሩ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች በፈረቃዉ ዉስጥ በአግባቡ መተግበራቸዉንና ዉጤታማነታቸዉን ይከታተላል፤ያረጋግጣል፤ተገቢ የማሻሻያ ስራዎችም እንዲተገበሩ ያደርጋል፤በየጊዜው የምርት ሂደቱን በማሻሻል ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር ያደርጋል፡፡ 13. የመስሪያ ማሽኖች ደህንነትና እንክብካቤ ስርዓት ዉጤታማ እንዲሆን በስራ ላይ እያሉ እና በፈረቃ ስራ ማጠናቀቂያ ጊዜ በተቀመጠዉ የማሽን ደህንነት አጠባበቅ እና ጽዳት እቅድ እና አሰራር መሰረት በአግባቡ መያዛቸዉን፤መጸዳታቸዉን መከታተል፤ማረጋገጥ እና ክፍተቶች ካሉ በፍጥነት የእርምት ስራዎችን ማከናወን፡፡ 14. እና ሌሎች ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎች ማከናወን * ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ በኢንደስትሪያል፤ ኬሚካል፤ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኤሌክትሪካል ምህንድስና ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች * በሙያው መስክ 8 ዓመት ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 4 ዓመት በፋብሪካ ውስጥ በተመሳሳይ ኃላፊነት የሰራ/ች