የሪል እስቴት ሽያጭ ባለሙያ
Hukaeb Trading PLC
- Job type
- Full-time
- Experience
- Junior
- Category
- Sales and Promotion
Job description
ስለ ድርጅቱ
ማሳለጫ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ ዘመናዊ የንግድ ሱቆችና የመኖሪያ ቤቶችን በማልማት ላይ ያለ ኩባንያ ነው። ድርጅቱ ለደንበኛ ጥራት ያለው አገልግሎት
የሚሰጡ፣ የሽያጭ ዒላማ ማሳካት የሚችሉ፣ ታማኝና ውጤታማ የሪል ስቴት ሽያጭ ባለሙያዎችን መቅጠር ይፈልጋል።
የሥራው ዋና ዓላማ
የቤትና የሱቅ ገዢዎችን በንቃት መፈለግ፣ ፕሮጀክቱን በሙያዊ መንገድ ማስተዋወቅ፣ የሽያጭ ሂደቱን ከመጀመሪያ የደንበኛ ግንኙነት እስከ ውል፣ ክፍያና
ርክክብ መከታተል እና የተሰጠውን የሽያጭ ዒላማ በድርጅቱ ደንብና ጥቅም መሠረት ማሳካት ነው።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
* ሊሆኑ የሚችሉ የቤትና የሱቅ ገዢዎችን እንዲሁም ተከራዮችን መለየት፣ ማነጋገርና በሙያዊ መንገድ ማስተናገድ። * በሙያዊ ኔትወርክ፣ በደንበኛ ሪፈራል፣ በዲጂታልማህበራዊ ሚዲያ፣ በኤግዚቢሽንና በቀጥታ ግንኙነት አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት። * የደንበኛውን ፍላጎት፣ በጀት፣ የክፍያ አቅምና የፈለገውን የቤትሱቅ ዓይነት በመረዳት ተስማሚ አማራጭ ማቅረብ። * ለደንበኞች የፕሮጀክቱን አቀማመጥ፣ ዲዛይን፣ የዩኒት ስፋት፣ ዋጋ፣ የክፍያ ዕቅድና የርክክብ ሂደት ትክክለኛ ማብራሪያ መስጠት። * የፕሮጀክት ሳይት፣ የናሙና ቤት ወይም የሚሸጥየሚከራይ ዩኒት ጉብኝት ማቀድና ማካሄድ። * በድርጅቱ የጸደቀ ዋጋ፣ የክፍያ ዕቅድ፣ ቅናሽና የውል መመሪያ ውስጥ የሽያጭ ድርድር ማካሄድና ውል ለመዝጋት መሥራት። * የተመደበውን ወርሃዊና ዓመታዊ የደንበኛ ፍለጋ፣ የጉብኝት፣ የቦታ ማስያዝ፣ የሽያጭና የገቢ ዒላማ ማሳካት። * እያንዳንዱን የደንበኛ ግንኙነት፣ የመረጃ ምንጭ፣ ፍላጎት፣ የጉብኝት ቀን፣ የድርድር ሁኔታና ቀጣይ እርምጃ በየቀኑ በተደራጀ የደንበኛሽያጭ መዝገብ ማስገባት።
* የቦታ ማስያዝ፣ የሽያጭ ውል፣ የክፍያ ጊዜ ሰሌዳ፣ የቀሪ ሂሳብ፣ የሰነድ ማሟላትና የርክክብ ሂደት እንዲጠናቀቅ ከፋይናንስ፣ ከሕግና ከፕሮጀክት ክፍሎች ጋር መከታተል።
* ክፍያ በድርጅቱ ሕጋዊ የባንክ ሂሳብና ደረሰኝ ብቻ መፈጸሙን ማረጋገጥ። * የገበያ ሁኔታ፣ የተወዳዳሪዎች ዋጋ፣ የደንበኞች አስተያየትና ቅሬታ በመሰብሰብ ለኃላፊው ማቅረብ። * ዕለታዊ የደንበኛ ክትትል፣ ሳምንታዊ የሽያጭ እንቅስቃሴና ወርሃዊ የዒላማ አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ። * ከደንበኞች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት መገንባት፣ ከሽያጭ በኋላ አገልግሎትና ሪፈራል መከታተል። * የደንበኛ፣ የዋጋ፣ የውልና የድርጅት መረጃን በምስጢር መጠበቅና ድርጅቱን በሙያዊ ሥነ-ምግባር መወከል። የሥልጣንና የአፈጻጸም ገደቦች
* ያልተፈቀደ ዋጋ፣ ቅናሽ፣ ኮሚሽን፣ የክፍያ ሁኔታ፣ የግንባታ ማጠናቀቂያ ወይም የርክክብ ቀን ለደንበኛ ቃል መግባት አይቻልም። ማሳለጫ ሪል ስቴት ኃየተየግማ
የሪል ስቴት ሽያጭ ባለሙያ የቅጥር ማስታወቂያ ገጽ
* በድርጅቱ ሕጋዊ ውክልና ካልተሰጠ በቀር የሽያጭ ውል መፈረም፣ የድርጅቱን ማህተም መጠቀም ወይም ሕጋዊ ቃል መግባት አይቻልም። * ከደንበኛ ገንዘብ፣ የግል ኮሚሽን፣ ስጦታ ወይም ሌላ ጥቅም መቀበል፣ የጎን ስምምነት ማድረግ ወይም የድርጅቱን ደንበኛ ወደ ሌላ ግብይት መምራት ክልክል ነው።
* ለደንበኛ የሚሰጥ መረጃ፣ ብሮሹር፣ ዋጋ፣ የክፍያ ዕቅድና ሌላ የሽያጭ ሰነድ በድርጅቱ የጸደቀ መሆን አለበት። የአፈጻጸም መለኪያዎች
የደንበኛ ፍለጋና ክትትል፣ የሳይት ጉብኝት፣ የቦታ ማስያዝ፣ የውል መዝጊያ፣ የተሰበሰበ ገቢ፣ የደንበኛ መዝገብና ሪፖርት ጥራት፣ የደንበኛ እርካታ፣ የሥራ ሰዓትና
የድርጅት ደንብ አክባሪነት ዋና ዋና የአፈጻጸም መለኪያዎች ይሆናሉ።
የትምህርትና የሥራ ልምድ
* በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሪል ስቴት፣ በሽያጭ ወይም በተዛማጅ ዘርፍ ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ። * ቢያንስ ዓመት በሽያጭ ዘርፍ የሥራ ልምድ፤ በሪል ስቴት ሽያጭ የተረጋገጠ ልምድ ያለውያላት ተመራጭ ነው። * ቀደም ሲል ያሳካውንችውን የሽያጭ ዒላማ፣ የሸጠውንችውን የቤትሱቅ ብዛት ወይም የሽያጭ ዋጋ ሊያረጋግጥልታረጋግጥ የሚችልትችል። አስፈላጊ ብቃቶች
* ጠንካራ የመግባባት፣ የማቅረብ፣ የድርድር፣ የውል መዝጋትና የደንበኛ ግንኙነት ችሎታ። * በራሱሷ ተነሳሽነት የሚሠራትሠራ፣ በግብና በውጤት ላይ ያተኮረች እና ተጠያቂነት የሚወስድየምትወስድ። * በግልና በቡድን የመሥራት፣ ችግር የመፍታትና ለዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት የመስጠት ችሎታ። * የማይክሮሶፍት ወርድኤክሴል፣ የደንበኛ መዝገብና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እውቀት። * መልካም የሙያ ሥነ-ምግባር፣ ታማኝነት፣ ምስጢር ጠባቂነትና ድርጅቱን በአግባቡ የመወከል ችሎታ።