የሪል እስቴት ልማት፣ ፕሮጀክት ማኔጅመንትና ሽያጭ ኃላፊ
Hukaeb Trading PLC
- Job type
- Part-time
- Experience
- Senior
- Category
- Project Management and Administration
Job description
ስለ ድርጅቱ
ማሳለጫ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ የተቀላቀለ የንግድና የመኖሪያ ፕሮጀክት በማልማት ላይ ያለ ኩባንያ ነው። ኩባንያው አሁን እየተገነባ ያለውን ፕሮጀክት በጊዜ፣
በበጀትና በጥራት ማጠናቀቅ፣ የንግድ ሱቆቹንና የመኖሪያ ቤቶቹን ሽያጭ በብቃት መምራት እንዲሁም በቦታ ግዥ፣ በተመጣጣኝ ቅያሪልዋጭ ወይም በጋራ
ልማት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መጀመር ይፈልጋል።
የሥራው ዋና ዓላማ
የአሁኑን ፕሮጀክት በሙሉ መምራትና መከታተል፤ የሱቆችና የመኖሪያ ቤቶች ሽያጭን ከዕቅድ እስከ ውልና ክፍያ ሙሉ በሙሉ መምራት፤ ብቁ የሽያጭ ቡድን
መገንባት፤ እንዲሁም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከሀሳብ ማመንጨት፣ ቦታ ፍለጋ፣ የጋራ ልማትና የልዋጭ ድርድር ጀምሮ እስከ ዲዛይን፣ ፈቃድ፣ ፋይናንስ፣ ግንባታ፣
ሽያጭ፣ ኪራይና ርክክብ ድረስ ሙሉ ሂደቱን መምራት፣ መከታተልና ማስፈጸም ነው።
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
የአሁኑን ፕሮጀክት መምራት
* የፕሮጀክቱን የጊዜ፣ የወጪ፣ የጥራት፣ የግዥ፣ የሰው ኃይልና የገንዘብ ፍሰት ዕቅድ ማዘጋጀትና መከታተል። * መሐንዲሶችን፣ አርክቴክቶችን፣ አማካሪዎችን፣ ተቋራጮችን፣ ፎርማንን፣ አቅራቢዎችንና የቢሮ ክፍሎችን ማስተባበር። * የሥራ ፕሮግራም፣ የሥራ መጠንና ዋጋ ዝርዝር፣ የግዥ ዕቅድ፣ የክፍያ ጥያቄና የእድገት ሪፖርት መፈተሽና መከታተል። * የጊዜ መዘግየት፣ የወጪ መጨመር፣ የጥራት ጉድለት፣ የውልና የአቅርቦት ስጋቶችን ቀድሞ መለየትና መፍትሔ ማስፈጸም። * ለአመራሩ ሳምንታዊና ወርሃዊ የፕሮጀክት፣ የወጪ፣ የገቢና የቀሪ ሥራ ሪፖርት ማቅረብ። አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ማመንጨትና ማልማት * የሪል ስቴት ገበያ፣ የደንበኞች ፍላጎት፣ የቦታ አቅምና የከተማውን የልማት አቅጣጫ ማጥናት። * የመኖሪያ፣ የንግድ፣ የሆቴል፣ የፈርኒሽድ አፓርታማና የቅይጥ አገልግሎት ፕሮጀክት ሀሳቦችን ማመንጨት። * ተስማሚ ቦታዎችን፣ ባለይዞታዎችን፣ የጋራ ልማት አጋሮችንና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በንቃት መፈለግ። * የፕሮጀክት ጽንሰ ሀሳብ፣ የንግድ ሞዴል፣ የመነሻ በጀትና የትግበራ መንገድ አዘጋጅቶ ለአመራሩ ማቅረብ። የቦታ ግምገማ፣ የጋራ ልማትና የልዋጭ ድርድር * የቦታ ግዥ፣ የተመጣጣኝ ቅያሪልዋጭ፣ የጋራ ልማትና ሌሎች የልማት አማራጮችን ማጥናትና ማነፃፀር። * የቦታውን አካባቢ፣ ስፋት፣ የመንገድ ተደራሽነት፣ ዞኒንግ፣ የግንባታ ከፍታ፣ የፕላን ስምምነት፣ የግንባታ አቅምና የገበያ ዋጋ መገምገም። * ከባለይዞታዎች፣ ወኪሎች፣ ደላሎች፣ ገማቾች፣ አማካሪዎችና መንግሥታዊ ተቋማት ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን ሙሉ በሙሉ ማስተባበር። ማሳለጫ ሪል ስቴት ኃየተየግማ
የሪል ስቴት ልማት፣ ፕሮጀክትና ሽያጭ የቅጥር ማስታወቂያ ገጽ
* በጋራ ልማት የመሬትና የአልሚ ድርሻ፣ የሚሰጥ ቤትሱቅ፣ ስፋት፣ ፎቅ፣ ዋጋ፣ የጊዜ ገደብ፣ ዋስትና፣ ርክክብና የመዘግየት ኃላፊነት ላይ ድርድር መምራት። * በልዋጭ የሚሰጠውን የተጠናቀቀ ቤትሱቅና የሚወሰደውን ይዞታ በገለልተኛ ግምት፣ በሕጋዊ ሰነድና በታክስ ተጽዕኖ እንዲነፃፀር ማስተባበር። * የድርድር ቃለ ጉባኤ፣ የመነሻ ውልየመግባቢያ ሰነድ ሀሳብ፣ የውሳኔ አማራጮችና የአደጋ ግምገማ ለአመራሩ ማቅረብ። * በአመራሩ የጽሑፍ ፈቃድ መሠረት ድርድሩን እስከ ስምምነት ማጠናቀቅና የውል አፈጻጸሙን መከታተል። የሕግ፣ የይዞታና የቴክኒክ ማጣራት * የባለቤትነት፣ የይዞታ፣ የዕዳ፣ የእገዳ፣ የውርስ፣ የስም ዝውውርና የሊዝ ሁኔታ ከሕግ ባለሙያ ጋር እንዲጣራ ማድረግ። * የካርታ፣ የፕላን ስምምነት፣ የዞኒንግ፣ የግንባታ ፈቃድና የአጠቃቀም ገደቦችን ከቴክኒክ ባለሙያዎች ጋር ማረጋገጥ። * የስም ዝውውር፣ ወደ ሊዝ መቀየር፣ የጋራ ልማት ውልና የልዋጭ ርክክብ ቅድመ ሁኔታዎችን በዝርዝር መከታተል። * ሁሉም ማጣራት እስኪጠናቀቅ ድረስ የማይመለስ ክፍያ ወይም ሕጋዊ ቃል እንዳይገባ ማረጋገጥ። የአዋጭነት፣ ፋይናንስና ኢንቨስትመንት ጥናት * የሚገነባውን ስፋት፣ የአጠቃቀም ክፍፍል፣ የፕሮጀክት ደረጃና የልማት ጊዜ መገመት። * የቦታ፣ የዲዛይን፣ የፈቃድ፣ የግንባታ፣ የፋይናንስ፣ የግብይትና የታክስ ወጪዎችን ከባለሙያዎች ጋር ማስላት። * የሽያጭና የኪራይ ገቢ፣ ትርፍ፣ የገንዘብ ፍሰት፣ የካፒታል መመለሻ፣ የሁኔታ ለውጥ ትንተናና የፕሮጀክት ስጋት መተንተን። * የአዋጭነት ጥናትና የኢንቨስትመንት ውሳኔ ሰነድ አዘጋጅቶ ለአመራሩ ማቅረብ። ከዲዛይንና ፈቃድ እስከ ግንባታና ርክክብ * የፕሮጀክት የዲዛይን መስፈርት፣ የበጀት ጣሪያ፣ የትግበራ ፕሮግራምና የግዥ ስትራቴጂ ማዘጋጀት። * አርክቴክቶችን፣ መሐንዲሶችን፣ አማካሪዎችንና ተቋራጮችን በመምረጥና በውል ሂደት መሳተፍ። * ዲዛይኑ ከገበያ ፍላጎት፣ ከበጀት፣ ከሕግና ከታቀደው አገልግሎት ጋር መጣጣሙን ማረጋገጥ። * የፈቃድ፣ የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የግንባታ፣ የጥራት፣ የሙከራና የርክክብ ሂደቶችን በሙሉ ማስተባበርና ማስፈጸም። የአሁኑ ፕሮጀክት ሽያጭ፣ ኪራይና ግብይት * አሁን እየተገነቡ ያሉትን የንግድ ሱቆችና የመኖሪያ ቤቶች ሽያጭ በቀጥታ መምራት፣ መከታተልና ማስፈጸም። * የሽያጭ ስትራቴጂ፣ ዓመታዊወርሃዊ ዕቅድ፣ የዩኒት ሽያጭ ዒላማ፣ የገቢ ዒላማ፣ የተግባር መርሐ ግብርና የአፈጻጸም መለኪያዎችን ማዘጋጀት። * ብቁና ውጤታማ የሪል ስቴት ሴልሶችን ከሰው ኃይል ክፍል ጋር መመልመል፣ ለቅጥር ማቅረብ፣ ማሰልጠን፣ የሽያጭ ዒላማ መስጠትና አፈጻጸማቸውን መገምገም።
* የሽያጭ ቡድኑን ዕለታዊ እንቅስቃሴ፣ የደንበኛ ጥሪ፣ የሳይት ጉብኝት፣ የድርድርና የውል መዝጊያ ሂደት መምራትና መከታተል። * ለሽያጭ ቡድኑ ቀጣይነት ያለው የምርት ዕውቀት፣ የሽያጭ፣ የድርድርና የደንበኛ አገልግሎት ሥልጠና፣ ድጋፍና ማበረታቻ መስጠት። * የቀጥታ ሽያጭ ቡድንን፣ የውጭ ሴልስ ኤጀንሲዎችን፣ ደላሎችን፣ ዲጂታል ማርኬቲንግንና የማስታወቂያ አጋሮችን ማስተባበር። * በሙያዊ ኔትወርክ፣ በዲጂታል ሚዲያ፣ በደንበኛ ሪፈራል፣ በኤግዚቢሽንና በቀጥታ ግንኙነት አዳዲስ ገዢዎችን ማፍራትና የደንበኛ መረብ ማስፋት። * በገበያ ጥናትና በተወዳዳሪዎች ትንተና ላይ የተመሠረተ የመሸጫ ዋጋ፣ የክፍያ ዕቅድ፣ የቅናሽ ወሰን፣ ኮሚሽንና የማስታወቂያ በጀት ሀሳብ ለአመራሩ ማቅረብ።
* የደንበኛ ፍለጋ፣ የፕሮጀክት ጉብኝት፣ የሽያጭ ድርድር፣ ቦታ ማስያዝ፣ ውል ዝግጅት፣ ክፍያ፣ ቀሪ ሂሳብና ርክክብ ሂደት በሥርዓት እንዲፈጸም ማድረግ። * ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ወይም ቁልፍ ደንበኞችን በቀጥታ ማስተናገድ፣ የሽያጭ ድርድር መምራትና በተፈቀደው የዋጋና የውል ወሰን ውስጥ ውል መዝጋት። * የደንበኞችን መረጃ፣ የሽያጭ ሂደት፣ የተያዙና የተሸጡ ዩኒቶች፣ ክፍያና ቀሪ ሂሳብ በተደራጀ መዝገብሲስተም እንዲያዝ ማድረግ። * የሽያጭ ውልና ቃል ኪዳኖች ከሕግ፣ ከፋይናንስና ከፕሮጀክት አቅም ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ማረጋገጥ። * የድርጅቱን ዋጋ፣ ትርፍ፣ የገንዘብ ፍሰት፣ ሕጋዊ ጥቅምና መልካም ስም ባስጠበቀ መልኩ ሽያጩን ማስፈጸም፤ ያልተፈቀደ ዋጋ፣ ቅናሽ፣ ቃል ወይም ውል እንዳይሰጥ መቆጣጠር።
* የሽያጭ አፈጻጸም፣ የደንበኛ ምንጭ፣ የግብይት ወጪ፣ የሽያጭ ለውጥ መጠንና የገቢ ሁኔታ ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርት ለአመራሩ ማቅረብ። ማሳለጫ ሪል ስቴት ኃየተየግማ
የሪል ስቴት ልማት፣ ፕሮጀክትና ሽያጭ የቅጥር ማስታወቂያ ገጽ
* ከደንበኞች ጋር ታማኝነት ላይ የተመሠረተ የረጅም ጊዜ ግንኙነት መገንባት፣ አስተያየትና ቅሬታቸውን ማስተናገድ፣ ሪፈራልና ተደጋጋሚ ንግድ ማሳደግ። * ከሽያጭ በኋላ የደንበኛ አገልግሎት፣ የውል ግዴታና ርክክብ እንዲፈጸም መከታተል፤ ያልተሸጡ ዩኒቶችን ለሽያጭ ወይም ለኪራይ የሚያበቃ አማራጭ ማቅረብ። የትምህርት መስፈርት
ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ በሪል ስቴት ማኔጅመንት፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት፣ ከተማ ፕላኒንግ፣ ፕሮጀክት ማኔጅመንት፣
ማርኬቲንግ፣ ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ ኢኮኖሚክስ ወይም ፋይናንስ ከጠንካራ የሪል ስቴት ልምድ ጋር። ሁለተኛ ዲግሪ ወይም ተዛማጅ ሙያዊ ሥልጠና ተመራጭ
ነው።
የሥራ ልምድ
* ቢያንስ ዓመት በሪል ስቴት፣ በፕሮጀክት ልማት፣ በኮንስትራክሽን ወይም ተዛማጅ ዘርፍ፤ ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ዓመት በአመራርፕሮጀክት ማኔጅመንት። * በመሬትይዞታ ግዥ፣ በቅያሪልዋጭ፣ በጋራ ልማት፣ በአዋጭነት ጥናት ወይም በሪል ስቴት ፕሮጀክት ልማት ተግባራዊና ሊረጋገጥ የሚችል ልምድ። * በአዲስ አበባ የይዞታ፣ የሊዝ፣ የዞኒንግ፣ የግንባታ ፈቃድ፣ የስም ዝውውርና የጋራ ልማት ሂደት ግንዛቤ። * ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ግንባታ፣ ሽያጭኪራይ ወይም ርክክብ ድረስ የመራው ፕሮጀክት ያለው ተመራጭ ነው። * የሪል ስቴት ሽያጭ ዕቅድ በማዘጋጀት፣ የሴልስ ቡድን በመገንባትና የሱቅአፓርታማ ሽያጭ ዒላማን በማሳካት ሊረጋገጥ የሚችል ውጤት ያለው። አስፈላጊ ብቃቶች
* ጠንካራ የፕሮጀክት አመራር፣ የድርድር፣ የችግር ፈቺነትና የውሳኔ አሰጣጥ ችሎታ። * የሪል ስቴት ገበያ፣ የአዋጭነት፣ የበጀት፣ የገንዘብ ፍሰትና የኢንቨስትመንት ትንተና። * የውል፣ የይዞታ፣ የሊዝ፣ የግንባታ ፈቃድና የግብር መሠረታዊ ግንዛቤ። * ከሕግ፣ ከፋይናንስ፣ ከኢንጂነሪንግ፣ ከሽያጭና ከመንግሥት ተቋማት ጋር የመሥራት ችሎታ። * የሽያጭ ቡድን አመራር፣ የዒላማና የአፈጻጸም መለኪያ አስተዳደር፣ የደንበኛ ድርድር፣ የደንበኛና የሽያጭ ሂደት መዝገብ ክትትልና የሽያጭ ሪፖርት ችሎታ። * ጠንካራ የሽያጭ ድርድርና ውል መዝጋት፣ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ደንበኞች ማስተናገድ፣ ቡድንን ማሰልጠንና ማበረታታት ችሎታ። * በግብና በውጤት ላይ ያተኮረ፣ በግፊት ውስጥ የሚሠራ፣ ችግር የሚፈታና ለውጤት ተጠያቂነት የሚወስድ አመለካከት። * የማይክሮሶፍት ኤክሴል፣ ወርድ፣ ፓወር ፖይንትና የፕሮጀክት ሪፖርት ዝግጅት ብቃት። * ጠንካራ የአማርኛና የእንግሊዝኛ የጽሑፍና የንግግር ችሎታ፤ ታማኝነት፣ ተጠያቂነትና ምስጢር ጠባቂነት።